2 ዓመት ሙሉ ዋስትና · ነፃ የሙያ ስልጠና · በአዲስ አበባ ነፃ ዲሊቨሪ
ዋና ገጽ ሁሉም ማሽኖች ስለ ZAG ZAG AI ረዳት ትዕዛዝ ይከታተሉ ድጋፍ ይዘዙ — Checkout አግኙን — WhatsApp

ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

ስለ ትዕዛዝ፣ ክፍያ፣ ማድረስ እና ዋስትና የተሰበሰቡ መልሶች።

እንዴት እዘዛለሁ?
ማሽኑን ከ“ማሽኖች” ገጽ ይክፈቱ → “አሁን ይዘዙ” ይጫኑ → ስም፣ ስልክ እና አድራሻ ይሙሉ → በCBE ወይም በቴሌብር ይክፈሉ → የግብይት ቁጥሩን (Txn ID) ያስገቡ → “ትዕዛዝ ይላኩ” ይጫኑ።
ክፍያ እንዴት ይፈጸማል?
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) ሂሳብ ቁጥር 1000091959104 ወይም በቴሌብር 0962983221 ይክፈሉ። ከከፈሉ በኋላ የግብይት ቁጥሩን በ checkout ላይ ማስገባት ግዴታ ነው። ደረሰኝ ስእል ማያያዝ አማራጭ ነው።
ማድረስ ስንት ቀን ይወስዳል?
በኢትዮጵያ ውስጥ ክፍያው ከተረጋገጠ በ48 ሰዓት ውስጥ ይደርሳል። በዌብሳይት ኦንላይን ለተከፈለ ትዕዛዝ ማድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ በነፃ ነው።
ከኢትዮጵያ ውጭ ትዕዛዝ ይቻላል?
አዎ። በDHL እና በሌሎች የማድረሻ አገልግሎት ሰጪዎች እንልካለን። የማድረስ ዋጋ በአገልግሎት ሰጪው ይወሰናል፤ ትክክለኛው ዋጋ ትዕዛዙን ስናረጋግጥ ይነገርዎታል። የጉምሩክ ቀረጥ በገዢው ይከፈላል።
የዋስትናው ሁኔታ ምንድን ነው?
ሁሉም ማሽኖች 2 ዓመት የአምራች ጉድለት ዋስትና አላቸው። በዋስትና ጊዜው ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት ጥገና፣ ስፔር ክፍል ማቅረብ ወይም ማስተካከል ብቻ ነው። ማሽን አይተካም፤ ገንዘብ አይመለስም።
ማሽን መመለስ እችላለሁ?
የተጠቀመ ወይም የተጫነ ማሽን አይመለስም። ደረሰኝ ከተቆረጠ በኋላም ተመላሽ ገንዘብ አይደረግም። ማሽኑ ሲደርስ የተጎዳ ከሆነ በ48 ሰዓት ውስጥ ፎቶ/ቪዲዮ ላኩልን — በዋስትናው መሰረት እናስተካክላለን ወይም ስፔር እንተካለን።
ክፍያዬ መቼ ይረጋገጣል?
በ24 ሰዓት ውስጥ እናረጋግጣለን። ማረጋገጫው ከተጠናቀቀ በ48 ሰዓት ውስጥ ማሽኑ ይደርሳል።
የትዕዛዜን ሁኔታ እንዴት አውቃለሁ?
የትዕዛዝ ቁጥርዎን (ለምሳሌ ZAG-26-0004) ይዘው በWhatsApp ወይም በስልክ ይጠይቁን። ትዕዛዝ ሲመጣ በቴሌግራም ማሳወቂያም ይደርሰናል።
ስፔር ክፍል ያገኛል?
አዎ። ለዋስትና ጊዜው የሚያስፈልጉ ስፔር ክፍሎች አሉን። የማሽኑን ዓይነትና የትዕዛዝ ቁጥር ይዘው ያግኙን።
የክፍያ ደረሰኝ ማያያዝ ግዴታ ነው?
አይደለም። Txn ID ብቻ በቂ ነው። ደረሰኝ ስእል ካያዙት ማረጋገጫው ፈጣን ይሆናል። ስእሉ ከድረ-ገጽ ውጭ በደህንነት ይቀመጣል።

መልስ አላገኙም?

በWhatsApp ወይም በስልክ ይጠይቁን — በፍጥነት እንመልሳለን።